በኮርፖሬሽኑ ሥር የሚገኘው አዳሚ ቱሉ የፀረ-ተባይ ማዘጋጃ ፋብሪካ የጥራት አስተዳደር (ISO 9001:2015) ሰርተፍኬት ባለቤት ሆነ፡፡
የአዳሚ ቱሉ የፀረ-ተባይ ማዘጋጃ ፋብሪካ የጥራት አስተዳደር (ISO 9001:2015) ሰርተፍኬት ስላገኘ እንኳን ደስ አላችሁ። ድርጅቱ በሥራ አመርር ሥርዓት ዓለም አቀፍ መመዘኛዎችን ሟሟላቱ በተከናወነው የኦዲት ሂደት ተገምግሞ የተሰጠው ሲሆን የተገኘው ውጤት አስተማማኝ ጥራት ያለው የፀረ-ተባይ ምርት ለገበያ የማቅረብ አቅማችንን በማጠናከር ለሀገሪቱ ግብርና እና ጤና ዘርፎች አፈጻጸም መሻሻል የሚኖረንን ሚና እንደሚያሳድግ ይታመናል፡፡ የሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ ከሶስት ወራት በፊት ተመሳሳይ ሰርተፍኬት ማግኘቱ የሚታወስ ሲሆን ኮርፖሬሽኑ በተሠማራባቸው ሌሎችም የሥራ ዘርፎች ላይ መሰል የጥራት ማረጋገጫ ውጤቶችን ለማግኘት ጥረቱን አጠናክሮ ይቀጥላል፡፡
